Tags » Ethiopian News

መንግስት ከምርጫው በፊት አፈናውን ያቆማል የሚለው ተስፋ መሟጠጡን ሂውማን ራይተስ ወች አስታወቀ

ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ባወጣው የ2014 አለማቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ላይ እንደጠቀሰው መንግስት ጋዜጠኞችን፣ ጸሃፊዎችን እና  የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችን እንደፈለገ  ያስራል፣ በሰላም ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ በወጡ ዜጎች ላይ ፖሊስ የሃይል እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲሁም ለማፈኛነት እየዋሉ ያሉትን በአለማቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የተወገዙትን አዋጆችን ለመለወጥ ምንም ምልክት አላሳየም ብሎአል።

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም ተቃውሞ ለማፈን መሞከሩን የገለጹት የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሌ ሌፍኮው፣ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ከሁሉም በባሰ እንደተሰቃዩና ከመጪው ምርጫ በፊት ሁኔታዎች ይሻሻላሉ የሚለው ተስፋ ሙሉ በሙሉ እንደተዳፈነ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እየፈጸመች ያለችው አስከፊ የሰብአዊ መብት ጥሰትን የለጋሽ አጋራትን አለመተቸታቸውን  ሂውማን ራይትስ ወች በሪፖርቱ አመልክቷል።ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፎችን እንዳያደረግ መከልከሉ፣ በኦሮምያ ክልል በሚያዚያና ግንቦት ወሮች የጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው፣ የግንቦት7 ዋና ጻሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ህገወጥ በሆነ መንገድ የመን ውስጥ ተይዘው መሰጠታቸውና የታሰሩበት ቦታ አለመታወቁንም ገልጿል።

ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ጸሃፊዎች በጸረ ሽብር ህግ መከሰሳቸውን፣ የ6 ጋዜጣ አሳተሚዎች በተመሳሳይ ወነጀል መከሰሳቸውን የጠቀሰው ሂማውን ራይትስ ወች፣ መንግስት ዌብሳይቶችን መዝጋቱን እንዲሁም ስልኮችን በመጥለፍ መረጃዎችን እንደሚያሰባሰብ አትቷል።

በኦሞ ሸለቆ አካባቢ በርካታ ዜጎች ያለፍላጎታቸውና ተገቢው ካሳ ሳይከፈላቸው እንደሚፈናቀሉም ድርጅቱ አስታውቋል። መንግስት ተደጋጋሚ ወቀሳና ትችት ቢደርስበትም የጸረ ሽብር ህጉንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶችን ለመቆጣጠር የወጣውን ህግ ለመቀየር ፈቃደና አለመሆኑን የጠቀሰው ሂውማን ራይትስ ወች፣ የመንግስትን የልማት እቅድ የተቹ ሰዎች እስራትና ወከባ እንደሚያጋጥማቸው አትቷል።

መንግስት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ማፈኑ በመጪው ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽኖ እንደሚኖረው ሌስሌ ሌፍኮው ተናግረዋል። ሂማን ራይትስ ወች በ656 ገጽ ሪፖርቱ በአለም ዙሪያ ያሉ የ90 አገራት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ቃኝቷል።

Ethiopian News

US urges Ethiopia to ensure fair trial to bloggers and journalists

US urges Ethiopia to ensure fair trial to bloggers and journalists

January 29, 2015

(U.S. Department of State) The United States is concerned by the Ethiopian Federal High Court’s January 28, 2015, decision to proceed with the trial of six bloggers and three independent journalists on charges under the Anti-Terrorism Proclamation. 160 more words

Ethiopian News

Boko Haram crisis: Chad 'captures Nigerian town from militants'

Boko Haram crisis: Chad ‘captures Nigerian town from militants’

Earlier this month, Chadian soldiers deployed to Cameroon’s border with Nigeria

Chad’s army has driven Boko Haram militants out of Malumfatori town in north-eastern Nigeria, a senior official from Niger has told the BBC. 408 more words

Ethiopian News

ሄሊኮፕተር በመያዝ ወደ ሶስተኛ አገር የጠፉት የአየር ሃይል ባልደረቦች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ

ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣  መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እና ቴክኒሻን ጸጋ ብርሃን ግደይ በተረጋጋ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለኢሳት ገልጸዋል።

ፓይለቶቹ በሚገኙበት ሶስተኛ አገር ውስጥ ሆነው ከኢሳት ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የነጻነት ትግል አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል።

ሶስታችንም በአንድ ላይ የምንመደብበትን ጊዜ ስንጠብቅ ቆይተን ነበር ያሉት ፓይለቶቹ፣ አጋጣሚው ሲፈጠርላቸው ቀደም ብሎ ባወጡት እቅድ መሰረት መጥፋታቸውን ገልጸዋል።

ጉዞአቸውን ወደ ሶስተኛ አገር በሚያደርጉበት ወቅት ከራዳር እይታ ውጭ ለመሆን እስከ 10 ሜትር ድረስ ዝቅ ብለው መብረራቸውን የገለጹት ፓይለቶቹ፣ ካሰቡበት ቦታ ሲደርሱ ነዳጃቸው ማለቁን ተናግረዋል።

ለምን ወጣችሁ ተብለው የተጠየቁት ፓይለቶቹ፣ በአየር ሃይል ውስጥ የሚታየው ዘረኝነት፣ አድልዎና የአስተዳደር መበላሸት ይህን ውሳኔ እንዲወስኑ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል።

እድሉ ቢገኝ አብዛኛው የአየር ሃይል አባል ስርአቱን ትተው ለመውጣት ዝግጁ መሆናቸውን ፓይለቶቹ ገልጸዋል። ፓይለቶቹ ሁኔታዎችን አመቻችተው ለኢሳት ቃለምልልስ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ የኢሳት የጋዜጠኞች  ኤርትራ በተገኙበት ወቅት በተለያዩ ወራት ኤርትራ የተገኙነትን በርካታ የአየር ሃይል አባላት አነጋግረዋል።

የሱ 27 እና የሚግ 23 አብራሪዎችን ጨምሮ በርካታ የተዋጊ ሄሊኮፕተር ፓይለቶች ኤርትራ ከሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በመቀላለቀል በመታገል ላይ ናቸው። ኢሳት ከፓይለቶች ጋር ያደረገውን ቀለምልልስ በቅርቡ ይለቃል።

Ethiopian News

አንድነትና መኢአድን ለእነ ትግስቱ አወሉና ለእነ አበባው መሃሪ ሰጠ

 አንድነትና መኢአድን ለእነ ትግስቱ አወሉና ለእነ አበባው መሃሪ ሰጠ

• ‹‹እውቅናውን የሰጠነው ለቦርዱ ለሚታዘዘው ነው›› ፕ/ር መርጋ በቃና

ምርጫ ቦርድ አንድነትን ለእነ ትግስቱ አወሉ፣ እንዲሁም መኢአድን ለእነ አበባው መሃሪ መስጠቱን ዛሬ ጥር 21/2007 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ፡፡ ምርጫ ቦርድ በመግለጫው ‹‹የእነ በላይ በፍቃዱ ቡድን›› በጠቅላላ ጉባኤ እንዳልተመረጠ፣ አምስት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት እንዳልመረጠ፣ የተመረጡበትም 51 ሲደመር አንድ መርህ አለመሆኑን፣ ጠቅላላ ጉባኤ ሲያደርግ ሪፖርት አለማድረጉንና ለአባላቱና ለፓርቲው ክብር የሌለው በመሆኑ ፓርቲውን ማስቀጠል እንደማይችል ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የትግስቱ አወሉ ቡድን መርህ ይከበር እያለ እየታገለ በመሆኑ፣ የኢ/ር ግዛቸው ካቤኔ አባላት ተገፍተው የወጡ በመሆናቸው፣ ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ለቦርዱ ሪፖርት እንዳደረጉ፣ ‹‹የእነ በላይ ቡድን›› ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንጂ እነሱ ችግራቸውን በውይይት ለመፍታት ፈቃደኛ በመሆናቸው እንዲሁም ለአባላቶቻቸውና ለፓርቲው ክብር ስላላቸው እውቅናውን ለእነሱ ሰጥቻለው ብሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ በመግለጫው ‹‹ምርጫ የሚገባ ፓርቲ በማስፈለጉ፣ ‹‹የእነ በላይ ቡድን ፓርቲውን የሚያስቀጥለው ባለመሆኑና ፓርቲውን እንደ ፓርቲ እንዲቆይ ስለሚፈለግ ዛሬ ጥር 21 ቦርዱ ባደረው አስቸኳይ ስብሰባ እነ ትግስቱ አወሉ ወደ ምርጫ እንዲገቡ ወስኗል›› ብሏል፡፡

ፕ/ር መርጋ በቃና ‹‹የእነ ትግስቱ አወሉ ቡድን ያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የተሟላ ስለመሆኑ በምን ታረጋግጡልናላችሁ?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ሁለቱም ችግር አለባቸው፡፡ እኛ ያየነው በአንጻራዊነት ነው፡፡ የእነ ትግስቱ አወሉ ቡድን ችግር ቢኖርበትም ከዛኛው የተሻለ ነው፡፡ እውቅናውን የሰጠነው ለቦርዱ ለሚታዘዘው ነው፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ እነ ማሙሸት አማረ በጠቅላላ ጉባኤ ባለመመረጣቸው፣ ለተከታታይ 3 ወራት ወርሃዊ መዋጮ ያላወጣ አባል ከአባልነት የሚሰረዝ በመሆኑና ከፓርቲ አባልነትም ስለተባረሩ እንዲሁም ህገ ወጥ ማህተም በማሳተማቸው እውቅና እንዳልሰጣቸው ገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል 2005 ዓ.ም ላይ አበባው መሃሪ የተመረጡበት ጠቅላላ ጉባኤ የተሟላ እንዳልነበር ቢታመንም በተደረገ ምርመራ የተሟላ መሆኑ በመታወቁ፣ በትክክለኛው ማህተም ስለሚጠቀም፣ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጉ በተባለበት ወቅት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረጉና ሪፖርቱንም ስላቀረበ ወደ ምርጫው እንዲገባ ወስኛለሁ ብሏል፡፡

Ethiopian News

አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ

በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!!

Ethiopian News

4 መኮንኖች ታሰሩ * የመከላከያ ሰራዊቱ ጥያቄ ወደ አመጽ ሊሸጋገር ተቃርቧል

4 መኮንኖች ታሰሩ * የመከላከያ ሰራዊቱ ጥያቄ ወደ አመጽ ሊሸጋገር ተቃርቧል


የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ካልደፈረሰ አይጠራም እያለ

ጨፍጫፊው ሌ/ጄነራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኩዋተር) የሚመራው ለሶማሌ ክልል ሰላም በሚል በአከባቢው የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የሕወሃት የጦር አዛዦች በራሳቸው የሚወሥዱት ውሳኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሱት ጫና እና እንዲሁም ሰራዊቱ ያቀረበውን ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ወደ አመጽ ማምራቱ ተሰምቷል::በጎዴ ከሚገኙ የመከላከያ ደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ካልደፈረሰ አይጠራም በሚል የተነሳውን አመጽ የተመለከቱ የሕወሓት የጦር አዛዦች የመከላከያ ሰራዊት ጥያቄ እና አመጻ ተከትሎ አነሳስተዋል የተባሉ አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ታውቋል::

በዚህም መሰረት
1.ሌተናት ኮሎኔል ተክለአረጋይ ዳኘው
2.ሻለቃ አበባየሁ አቡኑ
3.ሻለቃ ደምወዜ የኔአለም
4. የም/መቶ አለቃ ላቀው ልኬየለህ በጎዴ ወታደራዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል::

በጅጅጋ ከተማ በተከታታይ የሚሰበሰበው የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን በደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ የተነሳውን አለመተማመን እና ግርግር መቅረፍ እንዳልተቻለ እና አመጾች ሳይስፋፉ እና ስር ሳይሰዱ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሁሉ እንዲወሰዱ ሲል ተስማምቷል::በሶማሊ ክልል የሚገኘው የሕወሓት ጀሌዎች የሆኑ መኮንኖች በኦጋዴን ክልል ማህበረሰብ ላይ ይህ ነው የማይባል ከባድ ግፍ እና ግድያ እስር ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሲሆን በሕገወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት የሃገሪቷን አንጡረ ሓብት በመዝረፍ እና በማሳጣት ስራ ላይ መሰማራታቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው የሕወሓት የጦር መኮንኖች እንዲሁም በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሴቶችን በመድፈር በዘረፋ ከአከባቢው ሲቭል ባለስልጣናት ጋር የተመሳጠረ ሙስና በመስራት የሚከሰሱ ሲሆን ስርኣቱ በስልጣን እንዲቆይ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በአከባቢው እንደሚፈስ ምንጮቹ የተናገሩ ሲሆን የዚህ ገንዘብ ፍሰት የሙስና ተግባራት በሕወሓት የጦር መኮንኖች ይፈጸማል ሲሉ ይናገራል::

Ethiopian News