በ አዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ፖሊስ ከሰላማዊ ሙስሊሞች ጋር ተጋጨ

JULY 18, 2014 LEAVE A COMMENT

ዛሬ በአንዋር መስጊድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ የሆነ ሃይማኖታዊ ስነስርዓታቸውን እና ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ባሉበት ወቅት በተለምዶ ”አድማ በታኝ” እየተባሉ የሚጠሩ የፖሊስ አባላት  በሰላማዊ ዜጎች ላይ ድብደባ እና አፈሳ ማከናወናቸውን ከአንዋር መስጂድ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል።

እስከ አሁን ደረስ ፖሊስ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ ለማወቅ ባልችልም በርካቶች መደብደባቸውን እና ብዙዎች በፖሊስ መኪና ተጭነው መወሰዳቸውን ሰምቻለሁ።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ”ድምጻችን ይሰማ” እያሉ ለበርካታ ጊዜ እሪ ቢሉም ዛሬም የሚሰማ አካል አላገኙም። ቢሆንም ግን አልተሰማንም ብለው ዝም አላሉም። ተሰፋ ሳይቆርጡ አቤት በማለት ላይ ይገኛሉ።

ፖሊሶቻችን ሆይ እስከመቼ ደብድቦ አደር ትሆናላችሁ… ተው… ህዝብ ይበልጣል!