ቆንጂትና ተስፋዬ በወጣትነት እድሜያቸው ካደጉበትና የቤተሰባቸው ሐይማኖት የሆነውን እምነት ለቀው ወደ እስልምና ሲገቡ ሊያልፉበት ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቀውን ማህበራዊ፣ ቤተሰባዊ፣ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን በወጣትነት ትከሻቸው ተሸክመውት አልፈዋል፡፡ቤተሰቦቻቸውም የሚቻላቸውን ነገር ሁሉ አድርገው ወደነበሩበት ሃይማኖት ለመመለስ ስላልተሳካላቸው ሁኔታውን አምነው ተቀብለዋል፡፡ስጋ ነውና ወላጆች ልጅነታቸውን ወንድምና እህቶቻቸው ተመሳሳዩን ቆርጠው ሊጥሉት አልቻሉምና ከዚህ በፊት የነበራቸው ህይወት በሃይማኖት ዘርፍ ብቻ ተለይታ የድሮ ፍቅራቸው እንዳለ በነረበት ቀጥሏል፡፡ወላጆቻቸው ውስጣቸውን ሁሌም የሚከነክናቸው ጉዳይ በሁለቱም ቤተሰብ በኩል ተከስቷል፡፡መጠሪያ ስማቸው ወደ እነ ጀሚላ እና ሳላሃዲን ተቀይሯል፡፡ ሃይማኖታቸውን የቀየሩበትን ምክንያት ያቀረቡበትን ያህል ጠናካራ አመክንዩ(Logic) ስማቸውን በመቀየር ዙሪያ ግን ሊያቀርቡ አልቻሉም፡፡ቆንጂትም ተስፋዬም ወላጆቻቸው ስማቸውን ሲያወጡላቸው ያሉባቸውን ቤተሰባዊ ሁኔታና ልጆቹ ላይ ያዩትን አካላዊ ነገር አይተው ነው እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስማቸውን ያወጡላቸው፡፡ዛሬም ቢሆን ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም ጉድፈቱንም ይሁን ሰንካላነቱ አልታያቸውም፡፡ዛሬም ቆንጂት ለወላጆቿ ቆንጆ ናት ተስፋዬም እንዲሁ ለወላጆቹ ተስፋ ነው፡፡ታዲያ እነዚህ ሙስሊሞች ስማቸውን ለምን ቀየሩት ? 9 more words