Tags » Ethiopian News

ነገርን እንመርምር

በህወሓት አፍኝ ስርዓት የስለላ መረብ ውስጥ የህዝባዊ እምቢተኝነቶችንና ህዝባዊ አመፆችን መቆጣጠሪያና ማፈኛ መንገድ አንዱ እንደ ፌስቡክ ያሉ ነፃ መድረኮችን ተአማኒነት ማሳጣትና በራሱ መዘውር ውስጥ ማስገባት ዋና አካሄዱ ነው። የሀሰት መረጃወችን በራሱ ሰወች በማሰራጨት ፣ዳግም ውሸት ነው ፌስቡክን አትመኑ እያለ ያን የውሸት መረጃ ሼር ያደረገውን ማሸማቀቅና ተአማኒነቱን እንዲያጣ ማድረግ ተያይዞታል። ፌስ ቡክ ላይ የሚለቀቁ ፀረ ህወሓት የሆኑ መረጃወችን የሚከታተል አንድ ቡድን አለ። በተቻለ መጠን ተአማኒነት ያላቸውን አካውንቶች ለማጥቃትና በሃሰት መስመር ለማጥመድ ለእያንዳንዱ ታውቂ ሰው የተመደቡ ዋልጌወችም አሉ። ይሄ ሁኖ እያለ ነገሮችን መመርመር ካልቻልን ነፃ መድረካችንንም በህወሓት አፍኝ ቡድን እናስወርራለን ወይም ሙሉ በሙሉ እናስረክባለን ማለት ነው። በቅርቡ ፌቨን የምትባል የአዲግራት ልጂ(ከታች በፎቶው የምትታየው) በቆሸ የህወሓት ተንኮል ከተገደሉት ውስጥ ናት የሚል መረጃ ባንድ ዋልጌ ህወሓት ፌስቡከር ተለቆ አብዛኛውን የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዩጲያዊ ነፍስ ይማር ሲያሳዝን መቆየታቸው ልጂት በሀገረ ዱባይ በአፀደ ስጋ በስደት ያለች መሆኑ ተረጋግጧል። እንዲህና መሰል ጉዳዩችን በሀሰት የማር ወለላ ቀብተው መርዛቸውን ከሚተፋት የህወሓት ወያኔ የስለላ መዋቅሮች እንጠንቀቅ!ከስንዴው ውስጥ እንክርዳድ ፥ከማሩ ውስጥ መርዝ ፣ከእህሉ ጋር እንክርዳድ አለና ነገርን እንመርምር ።

በ እንቅዩጳዝዩን

Ethiopian News

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ህውሃት በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ከህውሃት ነጻ የመውጣት ፍላጎት ሙሉ በሙሉ መደፍጠጡን እያየን ነው

           ባለፈው አመት የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በኦህዴድና በብአዴን አካባቢ ራሳቸውን ከህውሃት ቀንበር ነጻ ለመውጣት ፍላጎት የሚያሳዩ፥ የወያኔን ፍጹማዊ የበላይነት በግልጽ የሚተቹ፥ አልፎ አልፎም የአቅማቸውን ያህል የህዝቡን ተቃውሞ ለመደገፍ ሙከራ የሚያደርጉ ካድሬዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረው ነበር።

         ለምሳሌ አባይ ጸሃይ ራሱ እንደመሰከረው የኦህዴድ የዞንና የወረዳ ካድሬዎች ከህዝቡ እኩል የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይተገበር እንቅፋት ሆነዋል ሲል ኮንኗቸው ነበር። በወቅቱ ምንም እንኳን እነዚህን ካድሬዎች “ልክ እናስገባለን” ተብሎ ቢፎከርም ልክ የገቡት ግን ፎካሪዎቹ እንደነበሩ እናስታውሳለን።

           በአማራ ክልልም ቢሆን የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ አቶ ገዱና ለእሳቸው ቅርበት የነበራቸው ብዙ ካድሬዎች የህዝቡን ጥያቄ ፍትሃዊነት ተቀብለው እንደነበር አንዘነጋም። በወቅቱ እነ አቶ ገዱና በርካታ ካድሬዎች በአንድ ወገን የአባይ ጸሃይ ፈረሶቹ በረከት ስምኦን፥ አዲሱ ለገሰ ካሳ ተክለብርሃንና አለምነው መኮንን በሌላ ወገን ሲሆኑ ደመቀ መኮንን ደግሞ በልጅነቱ ያመለጠውን ዥዋዥዌ ይጫወት እንደነበር የምንዘነጋው አይደለም (ደመቀ አቶ ገዱን ሲያገኘው የህዝቡ ጥያቄ ፍትሃዊ ነው እያለ ከእነበረከት ጋር ሲሆን ደግሞ የጸረ ሰላም ሃይሎች ጥያቄ ነው ይል ነበር)።

         እነ አይጋ በብአዴን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን መነቃቃት እንደ ትልቅ ድፍረት በመቁጠር “ጄላቲ እያስላስን ያሳደግነው ህጻን እንዴት ቢደፍረን ነው” በሚል አይነት እብሪት በትግሉ ወቅት የብአዴን ሚና ግጥም ማንበብ እንደነበረ ጽፈው እንዳስነበቡን የምንዘነጋው አይሆንም።

       ዛሬ ግን ብአዴንም ሆነ ኦህዴድ ለህውሃት መገበራቸውን በመግለጫዎቻቸው እየተናገሩ ናቸው። ኦህዴድ አስተዳድረዋለሁ በሚለው ክልል ውስጥ ከሶማሌ ክልል የመጡ ታጣቂዎች ያሻቸውን ሲያስሩ፥ ያሻቸውን ሲገድሉ፥ ያሻቸውን ያህል ሴት እህቶቻችንን ሲደፍሩ እያየና እየሰማ እንዲህ አይነት ግፍ በህዝብ ላይ አለመፈጸሙን ያለሃፍረት ሲያስተባብል እየሰማን ነው። ብአዴን ደግሞ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የጸረ ሰላም ሃይሎችና የትምክህተኞች ጥያቄ እንጂ የህዝቡ አይደለም ሲል ሰምተናል። ነገ ደግሞ ከህዝቡ የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችና የክልሉ ካቢኔ አባላት የትግራይ ክልልን ይቅርታ ለመጠየቅ መቀሌ ገቡ የሚል ዜና ሪፖርተር ላይ እናነብ ይሆናል።

        በተቃውሞው ጎራ ደግሞ የጎንደር ህዝብ በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የእኛም ደም ነው በማለቱ ተፈጥሮ የነበረ የተጠቂዎች መተሳሰብ (victims solidarity) ከኦሮሚያ የነጻነት ቻርተር በኋላ ወደነበረበት ተመልሶና ከትቢያ በታች ገብቶ ጎራ ለይተን እየተፏከትን እንገኛለን። እኛ የቱንም ያህል የተለያየ ራእይ፥ የተለያየ የፖለቲካ ግብ፥ የማይቀራረብ ትርክት እንዳለን አምነን ብንሻኮትም ለወያኔ ግን ያው አንድ አንድ ነን። ጠላቶች። ለወያኔ ፕሮፌሰር ብርሃኑም፥ ዶ/ር መረራም ኦቦ ጀዋርም ጠላቶች ናቸው። እንደው ሌላው ቢቀር ይህን መራራ እውነት እንኳ ተረድተን እንዴት መተሳሰብና መተባበር ያቅተናል? ወይስ የጎንደር ህዝብ ዳግም ካልነገረን የማይገባን ደንቆሮዎች ነን?

©Muluneh Eyoel Fuge

Ethiopian News

(ኢሳት ዜና - March 6, 2017)

— የአርበኛ ጎቤን ግድያ ተከትሎ ደስታውን ሲገልጽ የሰነበተው የጎንደር ከተማ ከንቲባ በነጻነት ሃይሎች ጥቃት ተሰነዘረበት።
— የህወሃት መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ በጎንደር ከተማ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ገብተዋል በማለት ከፍተኛ ፍተሻ አካሄዱ።
— በጂንካ ከተማ ሦስት የሙስሊም ሃይማኖት አባቶች ታሰሩ።
— የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት በኢትዮጵያ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲገደሎ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታስረዋል በሚል መግለጫ አወጣ።…

ኢሳት

Ethiopian News

Ethiopia: 5.6 million people need emergency food assistance

The failure of the 2016 October-December rains across parts of the Horn of Africa has led to a devastating drought in Somalia, south-eastern Ethiopia, and northern and eastern Kenya. 121 more words

Ethiopian-news

One Million Dollars’ Worth Ethiopian Manuscripts Donated to Catholic University

A recent donation of over one million dollars’ worth Ethiopian religious manuscripts to The Catholic University of America’s Semitics Department has opened up new research opportunities for students and professors studying the Christian Near East. 51 more words

Ethiopian-news

ከሮቤል ወሬ 〉ወደ ዱብ፡ ዱብ

ሀገር ሰላም ነው ብለን ውይ ይቅርታ ለካ ሀገር ሰላም አልነበረም፤ ኢንተርኔት ይሰራል ብለን የዜና መስኮቶቻችንን ስንከፋፍት የፌስቡኩ ወሬ ከሰላማዊ ሰልፍ ወደ ሮቤል ኪሮስ የዋና ውጤት ላይ አተኩሮ ነበር። ያው ዜናውን አነበብኩና ወደሌሎች አለማቀፍ ወሬች ሳመራ እዛም እርሱ ነው፤ በጣም ገርሞኝ ሳነብ ቆየሁ። አንዴ ባማርኛ ሌላ ጊዜ በእንግሊዝኛ የስድብና የትችት መዓት በሮቤል ኪሮስ ሀብቴ ላይ ሲወርድ በዓይኔ ሳነብ ከቆየሁ በኋላ እኔም በተራዬ ልክ ልኩን ብዬ የውስጤን አወጣሁና ወጣልኝ።

ከዛም መሸ፡ ነጋ፣ መሸ፡ ነጋ፤ ለካ ሀበሻውም ፈረንጁም አቤልን ሰድበው አልወጣላቸውም። በሮቤል ላይ ከተሰነዘሩት ትችቶች ያልተስማማሁበት ነገር አንድም የለም።

ከአቤል ትችቶች በጥቂቱ:

  1. ብቃት የሌለው የነፃ ዋና ተወዳዳሪ
  2. ኢትዮጵያን በየትኛውም ስፖርት መወከል የለበትም (ምናልባት ነፃ ትግል)
  3. ውክልናውን በዝምድና ማግኘቱ ደግሞ ይበልጥ ከሁሉ ታናሽ አድርጎታል
  4. ወዘተ

ከአቤል ድሎች ብቸኛው:

  1. የኢትዮጵያውያን የሁል ጊዜ የቀጫጫነት ተምሳሌት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ቦርጫምነት ቀይሮታል።

ለአቤል አምሳዮች (ለወንዶች ብቻ)

አቤልን ለመተቸት ብዙ ሊባል ይችላል፤ ነገር ግን ስንቶቻችን ነን የአቤልን አይነት የሰውነት አቋም ይዘን ለትችት የበቃነው? እንደው ስፖርት ከተሰራስ ስንት ጊዜ ሆነው? ጠዋት ተነስቶ ስፖርት የሚሰራውስ የትኛው የአዲሳባ ሰው ነው? ወይስ የየትኛው ዋሽንግተን ዲሲ ጂም ነው አባልነትህ?

ቢያንስ እንኳን አቆጣጠሩ ባይገባኝም ሮቤል በቀን (ጠዋት3000ሺ + ማታ 3000ሺ) = 6000ሺ ይሰራል። እንደብርሌ የተጎለተ ቦርጭ ተይዞ አቤልን ማንኳሰስ እጅጉን ከባድ ጥፋት ነው፤ ያው ስሜት አይሰጥማ ጃል። ፈረንጆቹ እኮ የአቤልን አይነት ሰውነት እንደጤና አይመለከቱትም፤ ለዛም በየቀኑ ስፖርት ቤት ይሄዳሉ፣ በየፓርኩ ይሮጣሉ፣ አመጋገብ ያስተካክላሉ፡ ወዘተ።

ፍልፍሉ በኢቢኤስ

ሀበሻው ግን የአቤልን አይነት ሰውነት እንደ ምቾትና የተሻለ ኑሮ ማሳያ ይመለከተዋል፤ ለዚህም አቤል ከአብዛኛው የሀበሻ የአዋቂ የሰውነት ቁመና ጋር የሚመሳሰለው።

ያው አቤል ኪሮስ እንደ ስፖርተኛና ሙሉ ሰውነቱ በካሜራ እንደሚቀረፅ ተወዳዳሪ የተስተካከለ ቁመና ቢኖረው የተሻለ ነበር። ነገር ግን ፈረንጆቹ በአቤል የሰውነት አቋም ላይ ካቀረቡት ትችት ልንማር የሚገባን የአብዛኛው የሀበሻ የአዋቂዎች አቋም ጤናማ ያይደለና በተለያዩ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ልናስተካክለው እንደሚገባን ነው። የአመጋገብ ስርዓታችንን ማስተካከል ደግሞ እጅጉን ተገቢ የሆነ መፍትሄ ነው ባይ ነኝ።

እንዲህ መካሪ ያደረገህ ማነው ካላችኑኝ፡ ቅጥነቴ ብዬ ልሰናበት።

News

የቄሳርን ለቄሳር የህዝብን ለህዝብ

ኢትዮጵያ የህዝብ መንግስት ያስፈልጋታል!

በ2007ቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በምርጫው ላይ ከፍተኛ ድምፅ አግኝቻለሁ እንዲያውም በትክክል 100% የህዝብ ደምፅ አገኝቻለሁ ሲል ቀልድ ወይም ‘አፕሪል ዘ ፉል’ መስሎን እውነተኛውን ዜና ስንጠብቅ ይኧው አንድ ዓመት አለፈን። ይባስ ብሎ አሸንጉሊት እና ማሰብ የተሳናቸውን ባለስልጣናት አበዛልን፤ መቸም ለዚህ ተመስገን አይባል። ☺በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በሀይማኖት እና በብዙ የተለያዩ መንገዶች ህዝብን ከህዝብ መለየት፣ ወዳጆችን ማጋጨት፣ ቂመኞችን በማበረታታና በማደራጀት በወገናቸው ላይ ግፍ እንዲፈፅሙ ማድረግ፤ በቃ በማንኛውም መንገድ ልዩነትን ማስፋት የሁልጊዜ አጀንዳው የሆነ መንግስት ይህችን ታላቅ እና ታሪካዊ ሀገር በብረት እየመራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ መንግስት አይደለም!

በቅርብ ጊዜያት ግን በተለያዩ መንገዶች በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንግስት እንዳልሆነ እየተመለከትን ያለንበት ሁሌታ ነው ያለው። ለዚህም ብዙም ሳንርቅ በኦሮሚያ ለአመታት እየተካሄደ የነበረው የህዝብ ጥያቄ (በሰላማዊም በአመፃዊም)፡ ትልቅ ማሳያ ነው። በተጨማሪም ከቅርቡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የህዝብ ድምፅ እየጎላና እየተስተጋባ ይገኛል። ለምሳሌ በጎንደር ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከንግር በላይ ነው፤ ምክንያቱም ህዝቡ መብቱን በሀይል ሲከለከል በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዬን ሳላሰማ አመለስም በማለት ወደ አደባባይ በመውጣት ተኝተው ለነበሩት የማንቂያ ደውል ተባባሪ ለፈለጉት ደግሞ መልካም ዜናን በማወጅ ለአዲሱ ሰላማዊ ትግል ትልቅ አስዋፅኦ አድርጓል።

መንግስት የህዝብ ነው፤ ህዝብ የመንግስት አይደለም።

የቄሳርን ለቄሳር የህዝብን ለህዝብ!ለጊዜው የቄሳሩን ትተን የህዝቡን እናውራው። ብሶት የወለደው የህወሓት ሰራዊት ሀገሪቱን ከወታደራዊው ደርግ በመንጠቅ ወደሌላ ወታደራዊ አገዛዝ ቀየረው። ለዚህም እንዲረዳው የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ይህችን ታላቅ ሀገር ከላይ በጠቀኳቸው መንገዶች ከፋፈላት፤ ይኧውም ለ25 ዓመታት በስልጣን ላይ ይገኛል። ከታሪካዊው የትግራይ ህዝብ የወጣው ነገር ግን ታሪካዊ ስሀተት እየሰራ ያለው መንግስት የአብላጫውን የትግራይ ህዝብ ሊወክል ይችል ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ምንም ክፋት የለውም። ነገር ግን በመላው ሀገሪቱ ላይ ለመግዛት እንዲመቸው ኢህአዴግ በሚል ሌላ ቅፅል ስም ወደ ምርጫ በመምጣትና በራሱ ማጣሪያ የተለያዩ ብሄሮችን ይወክላሉ ያላቸውን የህዝብ መሰል የፖለቲካ ፓርቲዎች በማቋቋም መንግስት መሰረተ፤ በአምስት አመት አንድ ጊዜ ደግሞ በራሱ ምርጫ አሸናፊነቱን እንዲነግረው የራሱ የሆነ የምርጫ ቦርድ አቋቋመ።በቃ ምን አለፋቹ ሁሌም ምርጫ አለ ሁሌም አንድ አሸናፊ አለ፤ ስሙም ህወሓት ይባላል። ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ሁሌም ቢሆን በጫካ ስሙ መጠራቱን ይወደዋል።ታዲያ የህዝብ ሊሆን የተገባው ነፃነት ላይ ማን እየተጠቀመበት ነው? ደም አፍስሰን ነው እዚህ የደረስነው ይሉናል፥ ታዲያ የህዝብን ደም ለምን ታፈሳላቹ? የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ነው የመጣነው ይሉናል፥ ታዲያ የየትኛውን ህዝብ ጥያቄ ነው የመለሳችሁት?ነው ወይስ የታላቋን የትግራይን መንግስት ለመመስረት በቂ የሆነ የህዝብ ቂም እያከማቻችሁ ነው?

የህዝብን ስልጣን ወደ ህዝብ!

የትግራይ ህዝብ የመረጣችሁ ምርጫ ኖሮት ሳይሆን ቋንቋውን የሚናገርለት ከራሱ ጓሮ የበቀለ የአመፅ ቡድን አንድ ብቻ ስለነበረ ነው፥ እርሱም ህወሓት ይባላል፤ ሲተነተን ህዝበ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፦ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ እንደማለት ነው። ስለዚህ አማራጭ አለበረም ቶሎ ተቀባይነት አገኘ። ነገር ግን በየጊዜው የተለያዪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከትግራይ ህዝብ የወጡ ነገር ግን በህወሓት የተደመሰሱ ብዙ ናቸው። ወደታላቋ ሀገራችን ስንመጣ ግን በተገኙት አጋጣሚዎች፣ ምርጫዎች፣ የህዝብ ስብሰባዎች ሁሉ መሪው መንግስት የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እና በሀይል ሲገዛ እንደኖረ ለማረጋገጥ የማይረሱ የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን መመልከት በቂ ነው።

በቃ ማለት በቃ ነው!

ይህ መንግስት አሁንም የህዝብን ድምፅ ለመስማት ዝግጁ አይደለም እንዲያውም እየጨቆነና ትላንት ካደረጋቸው የጭካኔ ተግባራት ይልቅ ብሶበት እና ጨምሮ እየተገኘ ነው፤ እንዲያውም ብዙዎች ካለፈው ወታደራዊ መንግት ጋር ያነፃፅሩታል። ሰሚ ካለ ይስማ፥ መንግት የህዝብ ነው እንጂ ህዝብ የመንግስት አይደለም።

የፅሁፉ ዋና አላማ የህዝብን ሀሳብ ለመጋራት እንጂ የየትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ሀሳብ ለመደገፍ አይደለም።

News