Tags » Ethiopians

የዘንድሮዋ ግንቦት 20 – እስክንድር ነጋ ፤ የሕሊና እስረኛ (ከቃሊቲ

ይኸው የወርሃ ሚያዝያ 2008ን የመጀምሪያ ሳምንት አገባደድን:: ግንቦት ተንደርድሮ እየመጣ ነው:: ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ጀምሯል:: ሩብ ምዕተ ዓመታትን በታላቁ ቤተመንግስት ማሳለፍ ቀላል አይደለም:: የአንድ ትውልድ ዕድሜ ነው:: እንኳን በተማሪዎች አብራክ ውስጥ ለተወለደ ድርጅት ይቅርና፣ በነባሮቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሚዛንም ረዥም የሥልጣን ዕድሜ ነው:: ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቆይታቸውን እንደጀብድ ለሚቆጥሩት የኢሕአዴግ ነባር መሪዎች፣ የዘንድሮዋ ግንቦት 20 በተለየ ሁኔታ ጮቤ የሚረገጥባት ናት::

Ethiopian People

በጋምቤላ ሁከቱ አይሏል | ፌደራል ፖሊስ ለሰልፍ የወጡትን ዛሬ ጋምቤላ ላይ በጥይት ቆላ

(ዘ-ሐበሻ) ጃዊ በሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ሁለት መሞታቸውን ተከትሎ; ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች 15 ኢትዮጵያውያንን (በአብዛኛው የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ) በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ተከትሎ የጋምቤላ ነዋሪ ትናንት ጀምሮት የነበረውን ሰልፍ ዛሬም ቀጥሎበት ውሏል::

ቁጥራቸው ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልፈኞች በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ; በስደተኞቹ ሴቶች ሳይቀሩ ብልታቸው ውስጥ እንጨት ተሸንቁሮ መገደላቸውን በማውገዝ ላይ በነበሩበት ወቅት የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ ሕዝቡን ለማስቆም ጥይት ተኩሷል:: ከጋምቤላ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክተው ፌደራል ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያውያኑ ሰልፈኞች ላይ በተኮሰው ጥይት እስካሁን የታወቁ 5 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል:: ከ15 በላይ ወገኖችም መቁሰላቸው ተሰምቷል::

በጋምቤላ በተለይ የኑዌርም ሆነ የአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት ያልሆኑትና በተለይም የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በስደተኞቹ ተመርጠው መገደላቸው ሕዝቡን ከፍተኛ ቁጣ ውስጥ ከመክተቱም በላይ ለ2ኛ ቀን አደባባይ ወጥቶ ውሏል:: ከስፍራው መረጃዎችን እንዳቀበሉን ወገኖች ገለጻ በአሁኑ ወቅት ጋምቤላ በፌደራል ፖሊስ ከመወረሯም በላይ ሰልፈኞቹ አልፈው ወደ ስደተኞች ጣቢያ እንዳይሄዱ መንገዶች መዘጋጋታቸውን ነው:::

በጋምቤላ ያለው ሁከት በቀጠለበት በዚህ ወቅት መንግስት ከአንድ ሳምንት በፊት በሙርሌ ጎሳ አባላት የተወሰዱትን 125 ህጻናት ጉዳይ መረጃ እስካለመስጠት ደርሷል:: የመንግስት ሚዲያዎች ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ታግተው የተወሰዱት ህፃናትና ሴቶች ያሉበትን ቦታ አውቆ ከቧሸዋል የሚል መረጃዎችን ያስተላለፉ ቢሆንም ከዚያ በኋላ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩና ህፃናቱም ታፍነው የተወሰዱበት ቦታ በረሃብና በበሽታ ከመጋለጣቸው አኳያ መንግስት ምን እያደረገ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ነው::

posted by tigi flate

Ethiopian People

የአማራ ምሁራን ፣ የወገናችሁን እርም ትበሉ ዘንድ እንዴት ተቻላችሁ?!

በቅርቡ የግል የምርምር ጥናቴን ለማካሄድ ፈለጌ፣ ይጠቅሙኛል ያልኳቸውን መረጃዎች ፍለጋ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን (CSA) ድረ-ገፅን ተመልከቼ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ ነበር ‘ 144 more words

Ethiopian People

የጋምቤላው ጉዳይ] ለዛሬ ደማችንን እንልሳለን | ከታምራት ነገራ

ከማንኛውም አደጋ ሊጠብቁን ሲገባቸው ከውስጣችን ሆነው የሚያጠቁንን ፤ ለጠላት አልሞ ተኳሽ አስተኳሽ የሆኑብንን ምን እንደምናደርግ ግራ ገባን እንጂ በውጭ ኃሎች መጠቃቱንም፤ የመጣውንም ኃይል መክቶ መመለሱንማ በሚገባ እናውቅበታለን፡፡ የውጭ ሚዲያ “በሊቢያ ኢትዮጵውያን እንደ ዶሮ ታረዱ” ብሎ ሲነግረን የኛው የእራሳችን የተባለው መንግስት ደግሞ “ሟቾቹ ኢትዮጵያውዊ መሆናቸው አልተጣራም” አለን፡፡ የሟቾች ፎቶ ሲመጣ አብረን ብይ ተጫውተን ፤ ጮርናቄ ተቃምተን ፤ቪዲዮ ቤት ተጋፍተን ያየነው አብሮ አደግ ጓደኞቻችን ሆነው አረፍነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የሱዳን ሚዲያዎች እራሳቸው “ጋምቤላ ውስጥ የተገደሉት ኢትዮጵውያን ቁጥር ከ 200 በላይ ነው” ብሎ ሲዘግብ የእኛው መንግስት “የሞቱት ቁጥር 140 አልበለጠም” ይለናል፡፡ በእኛ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ትክክለኛ መረጃ እንኳ ለማግኘት መንግስታችንን ማመን አቃተን፡፡

Ethiopian People

ለኦርቶዶክስ ኤግዚብሽን ማዕከል ይከላከላል ለሌላው ፓርላማም ይፈቀዳል | ቃልኪዳን ኃይሉ

የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳን ሳይ አንድ ተረት ትዝ አለኝ፡፡ “የሰፌዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ” የሚለው፡፡ ማለቴ እኔ በዚህ የጸሎት ስነ ስርአትና አምልኮ ጠብቄው የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንጂ አፈጉባኤውን ስላልነበረ ነው፡፡

Ethiopian People

የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት እያሰከተለ ያለው ጉዳትና ቀጣዩ አቅጣጫ

ከጊዜው ደረሰ ( gezew.derese@bell.net  

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ በሀገራችን ህልውና ላይ ከፈጸሙት ስህተቶች ሁሉ ትልቁ የሀገራችንን ታሪካዊም ይሁን ህጋዊ መብት ወደጎን በመተው በግል ውሳኔያቸው ኤርትራን በተመለከተ በአቶ ኢሳያስ የሚመራው ቡድን የጠየቃቸውን ሁሉ ያለአንዳች ማመናታት መስጠታቸው ነበር። በአወሮፓውያን አቆጣጠር 1994 የፈጸሙትን ስህተት ደግሞ በ1998 ማረም የሚያሰችላቸው ሁኔታ ቢፈጠርም ይህንን እድል ሳይጠቀሙበት  ሆን ብለው ማለፋቸው ብቻ ሳይሆን እንዲያውም እድሉን እንጠቀምበት ያሉትን ሁሉ በተለያየ የሀሰት ክስ በመክሰስ ፣ ማሰራቸው፣ ከስራ ማባረራቸው፣ ማሰቃየታቸው ወዘተ በታላቅ ምሬትና ሀዘን የሚታወስ በሀገራችንም ታሪካ እንደ ትልቅ ጠባሳ የሚቆጠር የታሪክ አሻራ ነው። ይህ መሰረታዊ ስህተት በሀገራችን ላይ እያደረሰ የሚገኘው አደጋ እስከዛሬም በብዙ መልኩ ለእድገታችንም ሆነ ለመሰረታዊ ህልውናችን አደጋ ሆኖ ይገኛል። በዚህ ጽሁፍ ይህ ስህተት ባሁኑ ስአት ከሚታየው ርሀብና በህዝባችን ላይ ከደረሰው አደጋ እንዲሁም ከመሰረታዊ የልማት ጉዞ አኳያ ያስከተለውን ተጽእኖ በመጠኑ አሳያለሁ።ይህንንም በማድረግ ከእርስ በእርስ ፍራቻ ተላቀን ፣ ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚል ስሜትን አስወግደን እያነዳንዳችን የፖለቲካ ልዩ ጠቀሜታ ሳይሆን ሀገርንና ህዝብን ለመታደግ ምን መደረግ እንዳለበት ለመነጋገር ተጨማሪ መንደርደሪያ ይሆናል ብየ አስባለሁ። 43 more words

Ethiopian People

ትግሉ ሰፊ የምሁራን ተሳትፎ ይሻል! – አርበኞች ግንቦት 7

ኢትዮጵያ በበብዛትም ይሁን በጥራት በውጭው አለምም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ምሁራን ያፈራች ሀገር ነች። በጅጉ የሚያሳዝነው ግን በሀገሪቱና በሕዝቧ ችግር ላይ ሀሳብ ሲሰጡ ፣ ባደባባይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የሚታዩት በጅጉ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ ነው ተከታታይ መንግስታት በምሁራን ላይ ያደረሱት ጥቃትና ማግለል ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ብዙዎች መከራን ከህዝብ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አጎንብሶ ማሳለፈን የመረጡበት ሁኔታ አለ። ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑም ለግል ጥቅማቸው ቅድሚያ በመስጠት ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር በመተባበር የሚሰሩ መኖራቸውም አይካደም። አብዛኛው ምሁራን በተለይም በብዙ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው ጭምር ሀገሪቱን ከገባችበት ማጥ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ እየተሳተፉ አይደለም። ይህ ዛሬ ባለው ችግርም ይሁን በታሪክ ፊት አሳዛኝ ነው።

ሀገራችን ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። የተማሩ ልጆቿ መላ እንዲመቱ በመጠየቅ ላይ ትገኛለች። ይልቁንም በሀገራችን ያለው ችግርና ሀገሪቱ እየሄደች ያለችበት መንገድና አቅጣጫ በተለይ ምሁራንን እንቅልፍ ሊነሰ ይገባል። ዕውነታው ከዚህም አልፎ የሀገሪቱን አሳዛኝና አደገኛ ሁኔታ ለመቀየር በሚደረገው ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ግድ ይላል። የመንግስት ግፍና ሰቆቃ በበዛበትና የሀገራችን ሕልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ሰዓት ምሁራን ላለመሳተፍ ምክንያት ማቅረብ የማይችሉበት ወቅት ላይ ደርሰናል። እንደማንኛውም ሀገር ምሁራን የኢትዮጵያ ምሁራን በሀገራችን ውስጥ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና ፍትሕ የሰፈነበት ስርዓት እንዲመሰረት ሊሸሹት የማይገባ ትልቅ ሚና አላቸው።

ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች መንግስት በልማትና በልማት እያመካኘ የሚያካሂደውን ሰፊ ዝርፊያ እንዲሁም ወያኔ ሩብ ምዕተ አመት ሙሉ በብሄረሰብ እኩልነት ስም እየማለ የሚያደርሰውን ያንድ ብሄረሰብ ጉጅሌ የበላይነት ማስፋፋት እምርረው በመታገል ላይ ናቸው። መስዋዕትነቱን እየከፈሉ የሚታገሉትና የሚወድቁ የሚነሱት ወጣቶችና ምስኪን ገበሬዎች ናቸው። እነዚህ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ሳይቀር ሲገብሩ በየቀኑ እየሰማንና እያየን ነው። ይህንን የህዝብ ጥያቄና ትግል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሁር ተመልካች ሆኖ ሊቀመጥ አይገባም። ትግሉን ከመምራት ጀምሮ እስከ ተራ ታጋይነት ባሉት ረድፎች ሁሉ ምሁራን ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል። ሰለትግሉ እቅጣጫም ሆነ ስለሀገሪቱ መጻዔ ዕድል ሃሳብ ማመንጨትና ማሰራጨት ይኖርበታል። ሀገራችን የደለቡ ችግሮቿን ተቋቁማ ፍትሕ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር የሚያደርጋትን የምህንድስና ስራ አስቀድሞ ማሰብና ማመቻቸት ይኖርበታል። ርግጥ ነው ይህን መሰል ተሳትፎ የሚያደርጉ ምሁራን አሁንም አሉ። ቁጥራቸው ግን ሊሆን ከሚገባው ጋር ሲወዳደር በጅጉ አነስተኛ ነው።

ምሁርነት ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ መቀዳጀት ብቻ እንዳልሆነ የታወቀ ነገር ነው። ምሁርነት ምሉዕ የሚሆነው መላውን የተፈጥሮ ከባቢ ከህዝብ ማህበራዊ ሕይወት ጋር አጣምሮ የሚያስብ አዕምሮን በዕውነት ላይ ለተመሰረተ ሀሳብና ዕውቀት ክብር መስጠትን ለተግባራዊነቱ መሟገትን የጨመረ ሲሆን ነው ። በመሆኑም ሁሌ እንደሚባለው ምሁርነት የጋን መብራትነት አይደለም። ምሁርነት በጨለማ ውስጥ ችቦ ሆኖ ብርሃን መፈንጠቅን ይመለከታል። ምስዋዕትነትንም ይጠይቃል።
ያለንበት ወቅት ለኢትዮጵያ ምሁራን ከፍተኛ ፈተናም ዕድልም ይዞ ቀርቧል። ይህ ልሽሽህ ቢሉት የማይሸሽ ፈተና ከመሆኑ ባልተናነሰ በታሪካችን እንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የጎላ አሻራን ለማኖርም ትልቅ የታሪክ ዕድል ነው። ይህ ፈተና ከፍተኛ ያርበኝነት ስሜትንና ሀላፊነት መውሰድን ይጠይቃል። አገር በተወሳሰበ ችግር ምክንያት ወደ አረንቋ እየገባች ምንም ሳይሰሩ መቀመጥ ወይም ዝም ብሎ ከመመልከት የበለጠ ለምሁር ሂሊና የሚከብድ ነገር ሊኖር አይችልም:: በጣም ላስተዋለ ሰው እንዲህ አይነት ዝምታ ሐጢያትም ነው። በእንዲህ አይነት ፈታኝ ወቅት የኢትዮጵያ ምሁራን ሀገሪቱን ወደተሻለ አቅጣጫ እንድትሔድ ላለመታጋል ምንም ምክንያት ማቅረብ አይችሉም። ሀሳብ የሚሰራጭባቸው የሀሳብ ክርክር የሚካሔድባቸው መድረኮች ፣ አደባባዮች ፣ የመገናኛ መሳሪያ አይነቶች የፖለቲካና የሲቪክ ማህበሮች ባገር ውስጥም በውጭም ያሉት መሳተፊያ ናቸው።

ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ምሁራን በሰፊውና እንደየፍላጎቶቻቸውና ችሎታቸው ሊሳተፉ የሚችሉባቸው በርካታ የትግል መስኮች አሉት። የሀገሪቱን ውስብስብ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የጥናት ውጤቶች ፣ ሀሳቦች ፣ ምክሮችም ሆነ ቀጥተኛ የምሁራን ተሳትፎ ለማስተናገድ አመቺ ሁኔታ ያለበት ድርጅት ነን። ወደፊትም የምሁራን ተሳትፎ እንዲጎለብት ሁኔታዎችን ይበልጥ ለማመቻቸት እንሰራለን። ዽርጅታችን የሀገራችን ችግር የሚወገደውና ዲሞክራሲና የዜጎች እኩልነት የሚረጋገጠው በበሰለና ከተራ ዜጋ እስከ ብስል ምሁራን በሚያከሂዱት ክርክርና የበሰለ ሃሳብ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያምናል። አሁን ያለው የሀገራችን ምሁራን ተሳትፎ ደረጃ ሁላችንም ከምንጠብቀው በታች በጅጉ ያነሰ መሆኑ ሁላችንንም ከማሳዘን አልፎ የሚያስቆጭና የሚያንገበግብ ሆኖአል:: አገርና ህዝብ ድረሱልኝ እያለ በሚጣራበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ማለፍ ይቻል ይሆናል። ይዋል ይደር እንጂ ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰበትን አፈናና ጭቆና እምቢኝ ብሎ ነጻነቱን ሲቀዳጅ ግን ከታሪክ ፍርድና ከህዝብ ትዝብት ማምለጥ አይቻለም።

አርበኞች ግንቦት 7 በአገር ውስጥም ሆነ በተለያየ ምክንያት በአለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ምሁር ለወገን ደራሽነቱንና አለኝታነቱን አሁኑኑ ይወጣ ዘንድ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

posted by tigi flate

Ethiopian People