Tags » Pdf

በመቀሌ የከተማ አሰተዳደር ስም በትግርኛ ቋንቋ ተጽፎ የተበተነው የህወሓት መግለጫ እንዲህ ይነበባል፤ Abrha Belay

“በአሁኗ ሰዓት አገራችን ኢትዮጵያ ወደ አደገኛ ወጥመድ እየገባች እንደሆነ የምንገነዘበውና ምስክር የማይሻ ሀቅ ነው። ሻእቢያ፣ ኦነግ እና ግንቦት 7 ግንባር ፈጥረው የትግራይ ህዝብንና ህወሃትን ለማጥፋት ተነስተዋል። የሸረቡት ሴራ የትግራይ ህዝብ ከመሪ ድርጅቱ ከህወሓት ነጥሎ ለመምታት ነው።

በዚህ መሰረት ለታወጀልን የጥፋት ድግስ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ መልስ መስጠት አስፈልጓል። ስለዚህ በፀረ-ሰላም እና ፀረ ትግራይ ህዝብ፣ እንዲሁም ህገ-መንግስቱን እየጣሱ ባሉ ኃይሎች ለሰኔ 16 በአ.አ. የጠሩትን ሰልፍ ለመቃወም ለመቀሌ ነዋሪ ህዝብ የአስቸኳይ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተደርጓል።

የሰልፉ ጥሪ በነገው እለት በትግራይ ስታድዮም ከጠዋቱ 12 ሰአት የሚጀመር ሆኖ፣ አላማውም የትግራይ ህዝብ ከድርጅቱ ከህወሃት እንደወትሮው ቆሞ፣ የጥፋት ኃይሎችን ሴራ ለማከሸፍ ነው።

ስለዚህ የመቀሌ ነዋሪ ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ነባር ታጋዮች፣ የጦር ጉዳተኞች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች በዚሁ በተጠራው ሰልፍ ላይ እንድትገኙ ይሁን” ይላል።

የኛ የህዝብ ልጆች ጥሪ ደግሞ –

በስምህ እየነገደ እንተን ገድሎ ለ27 አመት ሙሉ ስልጣን ላይ ተደላድሎ የኖረው ህወሓት የተባለው ድርጅት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የዲሞክራሲና የፍትህ ብርሃን ፍንጣቂን ለማጥፋት በስምህ “አስቸኳይ የሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ” ጥሪ እያቀረበ ይገኛል።
ህወሓት እንደሚለው በአንተው በትግራይ ህዝብ ላይ የተነሱ “የጥፋት ኃይሎች እንደሌሉ” አውቀህ በነገው እለት በመቀሌ በተጠራው ሰልፍ እንዳትገኝ እኛ ከአብራክህ የወጣን ልጆችህ ጥሪ እናደርጋልሃለን።

የአንተው ጠላት ህወሓት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም። ወይም በህወሓት የተዋረደው ኢትዮጵያዊነትን ወደ ክብር ቦታው ለማስመለስ ደፋ ቀና እያሉ ያሉትን ጠ/ምኒስተር አብይ አህመድ አይደሉም።

ህወሓት ዶ/ር አብይ አህመድ “የትግራይ ህዝብ ምንም የሌለው ደሃ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብና ህወሓት የተለያዩ ናቸው” ብለው ሀቁን ስለተናገሩ፣ በዚሁ ጉዳችን ወጣ ብሎ የተናደደው ህወሓት እንተን ይዞ መቀመቅ ለመውረድ እየተውተረተረ ይገኛል።

ይህን ወንጀለኛ ድርጅት “በኔ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ አቁም!” “አንት አገር ሻጭ፣ ትውልድ ገዳይ – ከፊቴ ጥፋ!” “ከኢትዮጵያዊው ወገኔ ጎን ቆሜያለሁ!” ብለህ የአልሞት-ባይ ተጋዳዩን ጥሪ በፉጹም ልብ ተቃውመህ የነስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ ካድሬዎች በጠሩት የጥፋት ሰልፍ ላይ እንዳትገኝ ይሁን!

ዶ/ር አቢይአህመድበሀውዜን ለተፈጸመው ጭፍጨፋ መታሰብያ መልዕክት አስተላለፉ። የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

በምስራቃዊ ትግራይ ትንሽ ከተማ በሀውዜን እንደ ሁሌውም የነጋችው የእለተ ረቡእ ጀምበር እንደሁልጊዜው ሆና አላለፈችም፡፡ ሰኔ 15 ቀን 1980 አ.ም ከረፋዱ 5 ሰአት ገደማ የሀውዜንን ሰማይ ይዞር የነበረው የሞት ሲላ 2 ሺህ 500 ንጹኀን ዜጎችን እንደወጡ ካስቀራቸው ይሄው ድፍን 30 አመት ሞላው፡፡ የእነዚያ ንጹሀን ወገኖቻችን እልቂት እሩብ ምእተ አመትን መሻገሩ እውን ቢሆንም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ህመሙን እና ሀዘኑን የዛሬ ያህል እየታመመ፣ የአሁን ያህል እያዘነ እና ለሁልጊዜውም እየዘከረ ዛሬ ደርሰናል፡፡ ለዛሬ ሀገራዊ አንድነታችን እና ኢትዮጵያዊ ህልውናችን ትናንት መሰረት ናት ስንል በሀውዜን የተሰዉት ኢትዮጵያውያን የማንነታችን እና የነጻነታችን መሰረቶች ናቸው ማለት እንጂ ሌላ ምንም ማለት አይደለም፡፡

መንግስት የህዝቡ ጥላ፣ ጠባቂ፣ አዳኝ እና የክፉ ጊዜ ከለላ ነው ከሚለው እሳቤ በፍጹም ተቃርኖ በሚገለጽ ጭካኔ እና አረመኔያዊ ድርጊት በመንግስታቸው የተጨፈጨፉት ውድ ዜጎቻችን ለትላንታችን ጸጸት ለነጋችን ደግሞ ትምህርት ሆነው ለዘለአለሙ ቢያሸልቡም በኢትዮጵያችን ታሪክ እና በህዝባችንም የክብር ልክ ውስጥ ሁሌም የምናነግሳቸው- መቼም የምናስባቸው ጀግኖቻችን ናቸው፡፡ የዚህች ሀገር ደግ ቀን እንዲነጋ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ እና በገዛ መንግስታቸውም ጭምር በእሳት አረር የቀለጡ በጭካኔ በትርም የተቀጠቀጡ እልፍ ሰማእታት ያሉን ህዝቦች ብንሆንም እነዚህን ባለውለታዎቻችንን አስታውሰን ከማመስገን፣ ከመዘከር እና በታሪካችን ማህደር ውስጥም ተገቢውን የክብር ስፍራ ከመስጠት አንጻር አሁንም ብዙ ይቀረናል፡፡

ከሀውዜን ሰማይ ላይ እሳት ዘንቦባቸው በሀውዜን ምድር ላይ አመድ ያደረጋቸውን ወገኖቻችንን እና በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት የጨካኞች መዳፍ ህይወታቸውን የነጠቃቸውን ወገኖቻችንን ይበልጥ ከማክበር፣ ከመዘከር እና ታሪካቸውን ከመከተብ ረገድ ሁሉም ዜጋ በተገቢው መንገድ የቤት ስራውን እንዲሰራ ጥሪዬን እያቀረብኩ መንግስትም ሰማእቶቻችንን በተገቢው ክብር ከፍ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ በሀውዜን በነበረው ዘግናኝ እልቂት የተፈጸመው ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ በትላንት ታሪክነቱ አስበነው የምናልፈው ብቻ ሳይሆን ዛሬ እና ነገም ይሄ እንዳይደገም ከራስ ጋር እንደሚገባ ቃልኪዳንም የምንቆጥረው ክቡር መስዋእትነት ነው፡፡

በዚያ የእልቂት እና የጥፋት ማእበል ውስጥ 2500 ወገኖቻችን በገዛ መንግስታቸው በአንዲት ጀምበር እንደዋዛ ከማለቃቸውም ባሻገር ከ600 በላይ የሚሆኑ አስከሬኖች በአንድ ጉድጓድ እንዲቀበሩ መደረጋቸው ሀዘናችንን እጥፍ ድርብ አድርጎት ልባችንን ሰብሮታል፡፡ ከረፋዱ 5 ሰአት እስከ አመሻሹ 11 ድረስ በዘለቀው እና 6 ሰአታትን ላስቆጠረው የሀውዜን የጥፋት መልእክት የተመደቡት 6 ወታደራዊ የጦር ሚጎች የመስቀል ቅርጽ እየሰሩ የሀውዜንን ሰማይ ሲናኙበትና ሞት ያንን ምድር ሲዞረው፤ ንጹሁ የሀገሬው ሰው ግና ገና መሞቅ የጀመረ ገበያ ላይ ነበር ቀልቡ እና ልቡ የነበረው፡፡ ያሰቡት ቀርቶ ያላሰቡት ለገጠማቸው እና አሰቃቂ በሆነ መልኩ ክፉ ጥፋት ለጎበኛቸው የሀውዜን ወገኖቻችን ፍቅራችን እና ክብራችን ወሰን የሌለው ቢሆንም ሀዘኑ ግን የሁልጊዜያችንም ነው፡፡

መንግስት ካለፈው ታሪክ ተምሮ እና የነገውንም ደግ ቀን በደግ እይታ አሻግሮ ትላንት የገጠመን መአት ከእንግዲህ እንዳይገጥመን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ በዚህ ታሪካዊ ቀን ላይ ቆሞ እንደገና ቃል ኪዳኑን ያድሳል፡፡ ያሰብነው ሁሉ የሚሳካው እና ከመጠፋፋት አዙሪት ወጥተን መልካም ሀሳባችን ፍሬ የሚያፈራው ህዝባችን ከመንግስት ጎን ቆሞ ጥሩውን በመደገፍ እና ልክ ያልሆነውንም በምክንያት በመንቀፍ መደጋገፍ ሲቻል በመሆኑ ሁላችንም በዚሁ አግባብ እንቆም ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ በዚያ ክፉ ቀን በንጹሀን ወገኖቼ ላይ በደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋም ሁሌም የሚሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እና የልብ ስብራት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

“ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!”
“ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ”
ዶ/ር አቢይ አህመድ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

As we have seen in past IAS exam, the questions can be based on data as old as 9 to 10 years.

But most of the questions are from the window of last 2 years current affairs. 193 more words

Prelims Cum Mains

ኢህአዴግ በኛ ጉዳይ፣ ከኛ ተደብቆ ይወስናል!! ኤልያስ

• ለወጣቶች ከተመደበው 10 ቢ.ብር ውስጥ 4 ቢ.ብር ሥራ ላይ አልዋለም
• ገዢው ፓርቲ፤ “ከአገርህ? ከሥልጣንህ?” ተብሎ ይጠየቅልን
• ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የምናተርፈውን በግልጽ እንወቀው

MANTUQ & MAFHUM

BAB I
PENDAHULUAN

A. Latar Belakang
Ketika kita berbicara mengenai ayat-ayat yang terkandung di dalam Al-Quran, sebenarnya dari semua ayat yang ada didalam Al-Quran tersebut tidak semuanya memberikan arti dan pemahaman yang jelas terhadap kita. 2,098 more words

Kurukshetra June Magazine : Resurgent Rural India

Download Kurukshetra Magazine June 2018 Issue: Resurgent Rural India-

Highlights: Towards Doubling Farmer’s Income by 2022, New Agriculture Schemes, Skill Development & Employment for Rural Youth, Education in Rural Areas, Road Networking in Rural, Rural Infrastructure, Agriculture, Telecom Connectivity, Women Empowerment, Children in India, Tackle Climate Change, Universal Health Coverage, Sanitation Roadmap… 71 more words

Uncategorised