Tags » // Quot

Dreams of Hope

“I know how men in exile feed on dreams of hope.”
Aeschylus

ለፈገግታ

አንድዛፍ ቆራጭ እባህር አጠግብ ያለ ዛፍ ላይ ወቶ እየቆረጠ ከጁ የሚቆርጥበት መጥረቢያ ያመልጠውና ባህር ውስጥ ይገባል ሰውየው በ ሁኔታው ተናዶ ሴለቅስ መልአክ ይገለጥለትና ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው ይለዋል መጥረቤዬ ከጄ አምልጥ ገባ ሲል መላኩ ወደ ባህሩ ይጠልቅና የወርቅ መጥረቤያ አውጥቶ ይሄ ነው ይለዋል ሰውየውም አይደለም ይላል ይቀጥልና አሁንም ከብር የተሰራ መጥረቤ ያወጣና ይሄስ ነው ይለዋል ሰውዬውም አይደለም ይለዋል በሦስተኛው የብረት መጥረቤያ አውጥቶ ይሄ ነው ሲለው አዋ ይላል ሰውዬው መላኩም ታማኝ ሰው በመሆንህ ብሎ ሦስቱንም መጥረቢያ ይሰጠዋል በደስታ ወደ ቤቱ ይሄድና ለሚስቱ ሲነግራት ቦታውን ካላሳየህኝ ብላው እያሳያት እያለ ሚስቱ ተንሸራታ ትሰምጣለች ባለበት ቆሞ ሲጮህ ያው መለአክ ይመጣና ምን ሆነህ ነው የምታለቅሰው ይለዋል ሰውዬው ሚስቴ ሰምጣብኝ ይላል መላኩ ወደ ባህሩ ይጠልቅና አንዲት በጣም ውብ የሆነች ሴት አውጥቶ ይቺ ናት ይለዋል ሰውዬው በፍጥነት አዋ ይላ መላኩ ተናዶ ለምን ትዋሻለህ ሲለው አይደለችም ብልህ ሦስት ሚስት አውጥተህ ልትሰጠኝ ነው አንዷንም አልቻልኳት፡፡
Source: 3ኛ ዓይን

Quot

አድዋ የማን

( ሄኖክ የሺጥላ )

ዳግማዊ ሚኒሊክ በእንጦጦ ማሪያም በኣቡነ ማቲያስ ኣንጋሽነት በመስከረም ፪፩ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሁለት ኣመተ
ምህረት የንጉሰ ነገስትነት ዘውዳቸውን መጫናቸውን ተከትሎ ለተለያዩ ኣውሮጳ ሃገሮች ለጻፉት ደብዳቤ የመጣለቸውን
መልስ እያሰላሰሉ ከዙፋናቸው ላይ ቁጭ ብለዋል። ንዴታቸው ግን ፊታቸው ላይ ኣይታይም።የታላቋ ብሪታንያና የጀርመን
መንግስታቶች የጃንሆይን መልእክት ተከትሎ በጻፉት ደብዳቤ
ሚኒሊክ ንግስናዋን ከርሶ በቀጥታ ሳይሆን ወኪሎ ኢንዲሆን በፈቀዱት በጣልያንና በመንግስቱዋ በኩል ነው መስማት
ያለብን የሚለው ነገር ፤ የንጉሱን ባለሙዋለች እጅጉን ያበሳጨ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን እቴጌይቱን ነበር
ያስቆጣው።
እቴጌ ጣይቱ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር የሚኖራትን ግንኙንት በኢጣልያን በኩል ታደርካለች የሚለው የጣልያንኛው
ድብቅ የኣተረጉዋጎም ሴራ ፤ ኣዋ የውጫሌ ውሉ፤ ከውሉም የ ፩፯ኛው ኣንቀጽ ፤ ብሎም ንጉስ ምኒሊክ እንዲስማሙ
ላማድረግ ተብሎ ከጣልያን መንግስት ከንጉስ ኡምቤርቶ የቀረበው የሊሬና የ መሳሪያ እርዳታ ንዴታቸውን ከሚቆጣጠሩት
በላይ ገፍው። እቴጌይቱ በርጋታ ከተቀመጡበት ብድግ ኣሉ

ኪነ-ህይወት

History Day!! --- Emperor Menelik II of Ethiopia (1844-1913) ---

Menelik II (August 17, 1844 – December 12, 1913),
Conquering Lion of Judah, Elect of God, King of Kings of Ethiopia was negus negust (emperor) of Ethiopia from 1889 to his death. 1,132 more words

ኪነ-ህይወት

(በእውቀቱ ሥዩም)

ትናንትና ማታ
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡

ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡

ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
(በእውቀቱ ሥዩም)

ኪነ-ህይወት

ልዑል ራስ መኮንን (አባ ኮራ/ አባ ቃኘው)

በአጤ ምንሊክ እና የሐረሩ ሹም በራስ መኮንን መካከል የነበረውን ዝምድና ለጠየቃችሁኝ ወዳጆቼ መልስ ይሆን ዘንድ በአለኝ መረጃ መሰረት በሁለቱ መሪወች መካከል የነበረው የስጋ ሳይሆን የጋብቻ ዝምድና ነበር, እንዲሁም ከልጅነት እስከእለት ዕልፈት ሳይለያዩ በመኖራቸው እና መወለደም ቋንቋ በመሆኑ ራስ መኮንን የአጤ ምንሊክ ታናሽ ወንድም ነበሩ በማለት ብዙ የታሪክ ጦማሪወች ጽፈዋል።

ከሸዋ ምድር የሚጠለቁት በመዕራባውያን አቆጣጠጠር በ1852 አንኮብር ጎራ ላይ ተወልደው ሐረርን ለ16 አመታት ያስተዳደሩት እና ከአደዋ ጦርነት ጀምሮ ለኢትዮጲያ ህዝብ ስፍር ቁጥር የሌላቸው በጎ ውለታወችን የዋሉት በ1906ዓም ላይ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ በድንገተኛ ህመም በ53 አመታቸው ህይወታቸው ያለፈው ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል ጉዴሳ ከሚኖሩበት ዘመን እና ህብረተሰብ ቀድመው የነቁ ስልጡን መሪ እንደነበሩ የተጻፈላቸውን የተለያዩ ጦማሮች አቅርቤ በተደጋጋሚ አስታውሼቸዋለሁ።

ከፊት ለፊት ያለውን ገደል ለመዝለል ወደ ኋላ መንደርደር አስፈላጊ ነውና እኛም አንዳንዴ ወደ ኋላ መለስ ቀለስ እያለን ለዚህ ዘመን ያበቁንን ያለፉትን አባቶችንን በክብር ማስታወሱ ይጠቀምናል እንጂ አይጎዳንም።

ንቁ ሰው ከታሪክ ፍቅርን እንጂ በቀልን አይወርስም።
Soutce: Eduardos-History-Page

ኪነ-ህይወት