Tags » Teddy Afro

ቴዲ አፍሮ ህዝቡ ከዶ/ር አብይ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረበ እኔም ከጎንዎ ነኝ ብሏል

ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬን እያቀረብኩኝ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነትን በማፈንና ብሄራዊ ስሜትን በማደብዘዝ አገራችንን ለአደጋ ከዳረገው ስርአት ለመላቀቅና በምትኩ አንድነትን ፥ መተባበርን እና ፍትህን ለማስፈን ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳን በተለያየ አቅጣጫ ብዙ እንቅስቃሴዎች በሚካሄድበት በአሁኑ ወቅት፦

በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን እና ይቅር መባባልን ይዘው ብቅ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና ባልደረቦቻቸው አጭር በሚባል የስልጣን ቆይታቸው ለወሰዶቸው በጎ እርምጃዎች እና ላሳዩን ኢትዮጵያዊ አለኝታነት አጋርነትን ማሳየት እና ከጎናቸው መቆም ጊዜው የሚጠይቀው አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ስገልፅ በሚደረጉት የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ላይ በሥራ አጋጣሚ በቦታው ባልገኝም በመንፈስ አብሬያችሁ መሆኔን ሳረጋግጥ በታላቅ ኢትዮጵያዊ ስሜት ነው።

ድል ለኢትዮጵያዊነት
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

Home

ኢትዮጵያን ወደ ፍቅር!!!

ባለፈዉ ዓመት ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የሰጠዉ ኣልበም ነው ፤የሙዚቃ ኣልበሙ ብዙ ነገሮችን በቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ እንዲሁም በሌሎች ላይ ይዞ የመጣ መሆኑ አይተናል።ጥቂቶቹን ብንመለከት ለዛሬ ፅሁፍ መንደርደሪያ ይሆናል።

ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በኤርትራ መዲና አስመራ የሙዚቃ ስራዎቹን ማቅረብ እንደሚፈልግ ገለጸ።

ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤ ኤፍ ፒ ቃለመጠይቅ የሰጠው ቴዲ አፍሮ በአስመራ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚፈልግ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ለመጪው የኢትዮጵያ የገና በዓል በአዲስ አበባ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ የአገዛዙን ፈቃድ በመጠበቅ ላይ መሆኑንም ኤ ኤፍ ፒ በዘገባው አመልክቷል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ሰሞኑን በድምጻዊ ቴስሮስ ካሳሁን ቤት ጎራ ብሎ ነበር።

ድምጻዊውን በሙዚቃዎቹና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያነጋገረበትን ቃለ መጠይቅም ለንባብ አብቅቷል።

የ41 አመቱ ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በቅርቡ ያወጣው ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበሙ በአለም አቀፉ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ተቀምጦ እንደነበር ኤ ኤፍ ፒ በዘገባው አስፍሯል።

ምንም እንኳን በቢልቦርድ ሰንጠረዥ ቀዳሚ ቦታን ይዞ የነበረ ቢሆንም ሙዚቃዎቹ ግን በሀገር ቤት በሚገኙ መንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፉ መታገዳቸውን ኤኤፍ ፒ በዘገባው ላይ አመልክቷል።

ድምጻዊው በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንደሆነም አትቷል።

ቴዲ አፍሮ በሙዚቃዎቹ በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን የሚሰብክ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ይህንንም እስከመጨረሻው እንደሚገፋበት በቃለምልልሱ ላይ ገልጿል።

ሙዚቃዎቹ አነጋግሪም ናቸው ።በብዙዎች ዘንድ የሚታወሱት የቴዲ አፍሮ ሙዚቃዎች በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ የሚተቹ ተደርገው ነው የሚወሰዱት ያለው ኤኤፍ ፒ በዚህም ምክንያት በአገዛዙ ባለስልጣናት ዘንድ በበጎ እንዲታይ አላደረገውም ሲል ያክላል።

በተለይም በአውሮፓውያኑ 2005 ላይ ያወጣው ጃ ያስተሰርያል የተሰኘው አልበሙ የተቃውሞ መዝሙር ተደርጎ ይወሰዳልም ይላል ዘገባው።

ደም ያፋሰሰው ምርጫ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት አልበሙ መለቀቁንም ያስታውሳል።

ይህን ያልወደዱት የአገዛዙ ባለስልጣናት ድምጻዊውን በጥርጣሬ እንደሚያዩትም አንስቷል።

በፈረንጆቹ 2008 በመኪና ሰው ገጭቶ በመግደል ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ለእስር የተዳረገ ቢሆንም የጥበብ አፍቃሪዎቹ ግን ጉዳዩ ፖለቲካዊ ምክንያት አለው ብለው እንደሚያምኑ ጠቁሟል።

በተደጋጋሚ ሊያቀርባቸው የነበሩት የሙዚቃ ዝግጅቶች እንደተሰረዙበት በቅርቡም የአዲስ የሙዚቃ አልበሙ የምርቃት ፕሮግራም በፖሊስ መታገዱንም አስታውሷል።

ለመጪው የገና በአልም የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ የአገዛዙን ባለስልጣናት ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ገልጿል።

የገና ዋዜማ አንድ ሳምንት የቀረው ቢሆንም እስካሁን ከአገዛዙ በኩል ምላሽ ስለመሰጠቱ የታወቀ ነገር የለም ብሏል ዘገባው።

በሌላ በኩልም ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በኤርትራ አስመራ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ ፍላጎት እንዳለው ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

በአስመራ የሙዚቃ ዝግጅቱን ማቅረብ ቢችል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ማሻሻል ይቻላል ብሎ እንደሚያምንም ድምጻዊው ተናግሯል።

የሚያስፈልገን የፍቅር፣ሰላምና ይቅር ባይነት ነው ያለው ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በሙዚቃ ስራዎቹ ይህን ማስተጋባት እንደሚችል ጠቅሷል።

ድምጻዊ ቴድሮስ እንዳለው ልጆች ሆነን የማስታውሰው ሁላችንም እንደ አንድ ህዝብ ነበር የምንኖረው፣ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ነበር የምናውቀው አሁን ግን በብሔር ማንነታችን ነው የምንለየው ይሄ ደግሞ በጣም አደገኛ እየሆነ መቷል።

ቴዲ አፍሮ መጪው ጊዜ በጣም እንደሚያሰጋውም ሳይገልጽ አላለፈም።

Latest News

“ሄዋን እንደዋዛ”

“ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ

በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ”

 

የሚላት የመጀመሪያዋን ቀዳማዊት ሄዋን ነው

 

“ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ

መጽናናያ ሆኖኛል፣ ክሶኛል ፍቅርሽ”

 

ሲል ደግሞ ይኽቺ ዳግማዊት ሄዋን እመቤታችን ማርያም ሆና፣ በልጇ በክርስቶስ እንደካሰችን ነው የሚያሳየው።

 

~ ቴዲ አፍሮ <3

 

“ልቤም ተደላደለ ጎኔም ደላው መሰለኝ

አንቺን ስለመውደዴ፣ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ

ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድን ነው?

ቢጠፋም ስሜ ነው።

በዚህች ዓለም ስኖር ሰው ነበር ረሀቤ

ምኞቴ ተሳካ ባንቺ አረፈ ልቤ…”

 

እያለ ነው እንግዲህ ዘፈኑ ጀምሮ……….

 

“ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ

በእኔና በምድር፣ ሞት እንዳመጣሽ

ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ

መጽናናያ ሆኖኛል፣ ክሶኛል ፍቅርሽ”

 

የሚለው ጋ የሚደርሰው። እንዲህ ቅልጥ ባለ እና ቅልጥ በሚያደርግ የፍቅር ዘፈን ላይ፥ ይኼ ማርያምን ነው የሚገልጸው ማለት ለምን እንደሚጠቅም አላውቅም። አንዳንዱ ነገር ባይብራራ ሳይሻል አይቀርም።

* * *

ጎሳዬ ተስፋዬ <3 “እናትዬ የሚለውን ለማን ነው የዘፈንከው?” ሲባል

 

“ለእናቴ” አለ ብለው ሲያነፍሩን ነበር። (ቃለ መጠይቁን አልሰማሁትም) እንግዲህ “ሁለት እናት አለኝ…” ሁሉ የሚል ሀረግ አለው። :)

 

እንግዲህ “አቤት ብቻ ነው ሲጣሩ እቴጌ!” ተብሏልና፥ የምንወዳቸው ከያንያን ሲሉን፣ አሉን ነው። ;)

* * *

የስዕል አውደ ርዕይ ልንመለከት ሄደን ሙንጭርጭር ያለ ስዕል እናይና፥ ቀለሙን ብቻ ወደነው እንኳን እንዳናልፍ ለነገር ሰዓሊው እዚያው ቆሞ እናገኘዋለን። …ዐይን ዐይኑን እያየን ትርጉሙን ከፊቱ ላይ ልንፈልግ ስናፈጥ፥ ማስረዳት ይቀጥላል።

 

“…እዚህ ላይ ቀዩ መስመር ህልማችንን ነው የሚወክለው። ወደዚያ የሄደው ሰማያዊ ደግሞ… ጥቁሩ መደራረቡ የሰዉን የኑሮ ውጣ ውረድ… እዚህ ጋ ደግሞ አይታይም እንጂ፣ ጽጌረዳ አበባው መድረቁ ህልም የመሰለችኝ ፍቅሬ ትታኝ መሄዷ…”

 

“አሃ” እያልን፣ ራሳችንን በአዎንታ እየነቀነቅን፣ በልባችን “ወንድሜ እኔ የማየው ነገር የለም” እንላለን።

 

የባሰም አለ፥ “ወንድም ይኽ ስዕል ምን ለማሳየት ነው?” ሲባል

 

“አይ ለራሴ ነው የሳልኩት”

 

ምንሼ አደባባይ ማውጣቱ?

እመው “ተከድኖ ይብሰል” ይሉትን ፈሊጣዊ አነጋገር ካለነገር አላሉትምና! አንዳንዱ ነገር ባይብራራ እና ከተሰራ በኋላ በመጣ እውቀት ለመቃኘት ባይሞከር እንዴት ሸጋ ነበር?!

 

ሰላም! 

ትዝብት

Teddy Afro (Tewodros Kassahun)

Tewodros Kassahun—known as Teddy Afro—is “the biggest star in Ethiopian musical history” (Gardner). Born July 14, 1976, Afro has released five albums, the most recent of which, … 1,535 more words

Biographies

The world loves Ethiopian pop star Teddy Afro. His own government doesn’t.

By Paul Schemm

Tewodros Kassahun (Teddy Afro) Photo Credit: Ethionewsflash.

ADDIS ABABA, Ethiopia — Monday marked the first day of the new Ethiopian year, but it hasn’t been much of a holiday for Teddy Afro, the country’s biggest pop star. 716 more words

News